ቅ. ሥላሴ ካቴድራል

{gallery}pic-cathedral{/gallery}

ቅ. ሥላሴ ካቴድራል

{gallery}pic-cathedral{/gallery}

ቅ. ሥላሴ ካቴድራል

{gallery}pic-cathedral{/gallery}

ቅ. ሥላሴ ካቴድራል

{gallery}pic-cathedral{/gallery}

http://www.trinity.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/46016501.jpg http://www.trinity.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/7472451.jpg http://www.trinity.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/395795church_4.jpg http://www.trinity.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/357816church_5.jpg
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጾመ ፍልሰታን አስመልክተው ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን

017

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  1.  በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ
  2.  ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ
  3.  የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችኹ
  4.   በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ
  5.  የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

የተወደዳችኹ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች ምእመናንና ምእመናት ልጆቻችን÷ እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለ፳፻፭ ዓ.ም. የቅድስት ድንግል ማርያም መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችኹ!!

‹‹ወኵሉ ዘሰአልክሙ በስምየ እገብር ለክሙ››፤ ‹‹በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርግላችኋለኹ›› ይላል የእግዚአብሔር ቃል፡፡ /ዮሐ.፲፬÷፲፫/

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ለተከታዮቹ ከሰጠን ስጦታዎች አንዱ የምንሻውን ኹሉ በስሙ እየለመን ጥያቄአችንን የማስፈጸሙ ጸጋ ነው፡፡ እርሱን በስሙ እየለመን የምንሻውን ሁሉ ማግኘት እንደምንችል ቅዱስ መጽሐፍ በብዙ ቦታ ደጋግሞ ያስረዳል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በቃል በተረዱትና በተማሩት ትምህርት መሠረት ይህን ጸጋ ወዲያውኑ በሥራ አውለውታል፤ የለመኑትንም አግኝተውበታል፡፡

እግዚአብሔር በባሕርዩ ፍቅር ስለኾነ፣ እኛ ሰዎች ፍቅር ኾነን፣ ፍቅርን መርሕ በማድረግ ስንለምነው መልሱ ይኹንታ እንደኾነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ኾኖ ቅድስት ድንግል ማርያምን በእናትነት ለቅዱሳን ሐዋርያት መስጠቱ የእናት ፍቅርና ክብር ከምንም በላይ መኾኑን ለማስረዳት እንደኾነ እንገነዘባለን፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ጌታችን ባዘዘውና ባስተማረው ትምህርት መሠረት የድንግል ማርያምና የሐዋርያት ፍቅር በልጅነትና በእናትነት ደረጃ ዘልቆአል፡፡ ሐዋርያዊት የኾነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ከጌታችን ከሐዋርያት የተቀበለችውን የቅድስት ድንግል ማርያም እናትነትና ክብር ጠብቃ በተግባር እየፈጸመች ትገኛለች፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅድስት ድንግል ማርያም ካረፈች በኋላ በመጀመሪያ ቅዱስ ሥጋዋ ያለበትን ኹናቴ ለማወቅ፣ በሁለተኛ ትንሣኤዋንና ዕርገትዋን ለማየት ባደረባቸው የፍቅርና የአክብሮት ጉጉት ፈጣሪያቸውን በጾምና በሱባኤ ለምነው የልመናቸው መልስ በጥያቄአቸው መሠረት ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ማየት ኾኖአል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ትልቁ ቁም ነገር እንደ ጌታ ቃል በፍቅርና በሰላም ኾነን የምንለምነውን ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አዎንታዊ መልስ የምናገኝበት መኾኑን ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ ዐሥራ አምስት ቀን ለሁለት ሱባዔ በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዐት የምትፈጽመው አምልኮተ እግዚአብሔር ይህን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

የተወደዳችኹ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼና ወገኖቼ ምእመናንና ምእመናት

ጾማችንና ጸሎታችን ከእግዚአብሔር ፊት ደርሶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ፍጹም ይቅርታና በረከት ሊያስገኝ የሚችለው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የጾምን እንደኾነ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው ጾም በሕገ ቤተ ክርስቲያን ከተከለከሉ መባልዕትና መጠጦች መከልከል ብቻ ሳይኾን÷ ለተበደለና ለተገፋ ፍትሕን መስጠት፣ ለተራበ ቆርሶ ማጉረስ፣ ለታረዘ ቀዶ ማልበስ፣ የተጣላውን ማስታረቅ፣ የተሳሳተውን መክሮና አስተምሮ መመለስ፣ በአጠቃላይ በማኅበረ ሰቡ መካከል ፍጹም ሰላምና ፍቅር፣ እኩልነትና ወንድማማችነት እንዲሰፍን ማድረግና የመሳሰሉት ሁሉ የጾም ወቅት ተግባራት ናቸው፡፡

በተለይም ስለ ሰላምና ፍቅር ስናስብ ከግለሰብ ጀምሮ እስከ አገር አቀፍ ከዚያም እስከ ዓለም አቀፍ ያለውን ሰላም ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ፣ ቀደም ብለው ካለፉት ዘመናት አሁን ያለንበት ዘመን የተሻለና ብሩህ ተስፋ የሚታይበት ቢኾንም፣ አሁንም ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ቁልፍና ሀገራዊ ተግባር እንዳለ ሳናስገነዝብ አናልፍም፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊ የኾነ ሁሉ ሃይማኖትና ቋንቋ ሳይከፋፍለው ለዘመናት የቆየውን ተፈቃቅሮ፣ ተከባብሮ በሰላምና በአንድነት የመኖር ጸጋችንንና ባህላችንን እንደ ዐይን ብሌን በመጠበቅ ወደ ጀመርነው የልማትና የዕድገት አጀንዳችን ብቻ እንድንመለከት ነው፡፡ ይህም እውን እንዲኾን የክርስቶስ ተከታይና የድንግል ማርያም ወዳጅ የኾነ ሁሉ አሁን በምንጀምረው ሱባዔ ፈጣሪውን ከልብ መለመን አለበት፡፡

በዚህ ዐይነት የምናቀርበው ጾምና ጸሎት የመጨረሻው ግቡ ፍቅርና ሰላም ስለኾነ ከእግዚአብሔር የምናገኘው መልስ ይኹንታ እንደኾነ በመገንዘብ ሁላችንም በሃይማኖት በመጽናትና ፍቅርን ገንዘብ በማድረግ መጾምና መጸለይ ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላምና የፍቅር ጾም ያድርግልን፡፡ አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.

 
በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ አረጋወያን ለ10ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ

                 በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ (Bsc)

“ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር ከክፉ ያድነዋል፡፡” መዝ. 40÷1

“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ”2ኛ ቆሮ. 9÷7

0025

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በድህረ ገፃችን አማካኝነት ወጣት ብሩክ አስራት የክርስትና ስሙ ግርማ ጽዮን ከዛሬ 10 ወራት በፊት ጀምሮ ለካቴድራሉ አረጋውያን የሚሆን በየወሩ ለአረጋውያኑ የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው ለ10ኛ ጊዜ ለ1 ወር የሚሆን በእነ ወ/ሮ ማርታ ወርቄ፤በወንድሙ እና በጓደኞቹ አማካኝነት እርዳታውን ልኳል፡፡

በዚሁ ዕለት በቄስ ይሄይስ ፈንቴ አማካኝነት ለወጣት ብሩክ አስራት፤ለቤተሰዎቹና ለጓደኞቹ ጸሎትና ምስጋና እንዲሁም ቃለ ምእዳን የተሰጠ ሲሆን በወጣት ብሩክ አስራት እየተደረገ ላለው ነገር ሁሉ ምስጋናቸው እጅግ የላቀ መሆኑን ገልፀው ሌሎችም የዚሁ የተቀደሰ ዓላማ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም መልአከ ሰላም ማሩ ለወጣት ብሩክ አስራትና ለቤተ ሰዎቹ እያደረገው ላለው ነገር ሁሉ በዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ስም ካቴድራሉን በመወከል ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡

እነዚህ አረጋውያን ከዛሬ 45 ዓመታት በፊት ከዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በንጉሱ አማካኝነት በካቴድራሉ በጎ አድራጎት /ምግባረ ሠናይ ክፍል ሥር በቃለ ዓዋዲ መሠረት የተቋቋመ ሲሆን ቀደም ሲል በብዙ መልኩ የተደራጀ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁንም በካቴድራሉ አስተዳደር አማካኝነት እንደቀድሞ ሁሉ ለማጠናከር ከፍተኛ የሆነ ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡

በመሆኑም በዘላቂነተ የአረጋውያኑ ችግር በመጠኑ ለመቅረፍ እንደ ወጣት ብሩክ አስራት የክርስትና ስሙ ግርማ ጽዮን አቅማችሁ የፈቀደውን/የቻላችሁትን ያህል እርዳታ እንድታድርጉ እናሳስባለን፡፡ አረጋውያኑ ከሚያስፈልጓቸው መሠረታዊ ነገሮች መካከል፡- 1. ምግብ፣ 2. መጠለያ፣ 3. ልብስና 4. ሞግዚት ናቸው፡፡

ወጣት ብሩክ አስራት ለእነዚህ አረጋውያን በየወሩ ለጤፍ 980 ብር ፣ ለዘይት 500 ብር ፣ ለበርበሬ እና ሽሮ 680 ብር፣ ለጋዝ 150 ብር፣ ስኳር 140 ብር፣ ሰሙና 86 ብር እና ለሻይቅጠል 50 ብር ድምር 2,586 ብር ሲሆን እስከአሁን ድረስ ለ10 ወር ለአረጋውያኑ ወጪ ያደረገው ገንዘብ 2,586 x 10= 25,860 ብር ለአረጋውያኑ ወጭጪ አድረጓል፡፡

 
አዲሱ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

                             በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ (Bsc)

0013

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ና በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ አማካኝነት ከሐምሌ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. ጀምሮ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ ሲሆኑ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባዔ፣ ካህናት፣ መዘምራን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና የአጥቢየው ምእመናን በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጐላቸዋል፡፡

ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ቀደም ሲል በአገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በተለያሉ ትላልቅ ገዳማትና አድባራት በዋና አስተዳዳሪነት ተመድበው ቤተ ክርስቲያኒቱን፤ማህበረ ካህናቱና ሕዝበ ክርስቲያኑን በአድነትና በስምምነተ ሲገለግሉ መቆየታቸው አብረዋቸው የመጡት የምስካዬ ሕዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም አስተዳዳሪ ከብዙ በጥቂቱ ተናግረዋል ፡፡

ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ ከዚህ በፊት በእልቅና/በዋና አስተዳዳሪት ያገለገሉባቸው ገዳማትና አድባራት፡-

1. በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም ቤ/ክ ፤

2. ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፤

3. መንበረ መንግስት ቅ/ገብርኤል /

4. ሱዳን እና አውትራሊያ ውስጥ የሚገኙ የኢ/ኦ/ተ/አብያተ ክርስቲያናት ሲሆኑ

5. ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዋና ዲን

6. በአሁኑ ሰዓት የእልቅና የመጨረሻ እድገት በሆነው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹሞዋል ፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የካቴድራሉ የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም የምስካዬ ሕዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም አስተዳዳሪና የመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ማህበረ ካናት የተገኙ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶም ከመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልና ከመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ሊቃውነት ቅኔ ቀርቧል፡፡

ዕለቱን አስመልክተው ጢሞቴዎስ አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የካቴድራሉ የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በበኩላቸው ቤተክርስቲያን አንዲት ናት፣ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ አባቶቻችን ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወሩ ቤተክርስቲያንና ህዝበ ክርስቲያንን ይመራሉ፣ ያስተምራሉ፣ ለዚህም ነው ዛሬ ሁለቱም አባቶቻችን (ወንድሞቻችን) ከመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወደ ደብረ ገነት መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤልና ከመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አንዲቷን ቤተክርስቲያን ለማገልገልና ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውን ለመፈፀም የተዛወሩት ብለዋል፡፡ምንም እንኳን የቦታው ስም ቢለያይም የቤተክርስቲያቱ አገልግሎት አንድ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡

ከዚሁ ጋር አያይዘውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ከያዙት መንፈሳዊ እውቀት በተጨማሪ ዘመኑ የደረሰበትን እውቀት በመቅሰም ቤተ ክርስቲያኒቱና ሕዝበ ክርስቲያኑ በተሻለ መልኩ ሊያገለግሉ ይገባል ፤ቤተ ክርስቲያኒቱም የመልካም ሥራ ባለቤት በመሆኗ ሙስና እና ብልሱ አሠራርን በማስወገድ ረገድ የበኩሏን አስተዋፅኦ በመጣት ላይ እንደምትገኝ አክለው ገልፀዋል፡፡

 
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለሥራ ኃላፊዎች የ3 ቀን የምክክርና የግንዛቤ ማስጨባጫ ሥልጠና ተሰጠ

                 “ክፉውን ነገር ተጸየፉት ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ”ሮሜ 12÷9

0003

መልካም አስተዳደር ለዘላቂና ሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሥልጠና የተጀመረው ሐምሌ 9/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ሥልጠናው እየተካሄደው ያለውም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንገል አዳራሽ ነው፡፡ በዚሁ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ሥልጠና ተካፋይ የሆኑ ሥራ ኃላፊዎች፡-

1. የሀገረ ሰብከት ሠራተኞች፣

2. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ፀሐፊዎች፣

3. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣

4. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የክፍል ኃላፊች፣

5. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ናቸው፡፡

ሥልጠናውን በፀሎት የከፈቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአ/አ/ሀ/ስ/የቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣንት በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የሥልጠናውን መርሃ ግብር የሚመሩት መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ ሲሆኑ ከፀሎቱ መርሃ ግብር በኃላ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአ/አ/ሀ/ስ/የቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀጳጳስ አማካኝት ስለ ሥልጠናው አስፈላጊነት በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም ከመንግስት ተወካይ አጠር ያለ ፀሑፍ ተነቧል፡፡ከዚህ በኋላ ወደ ሥልጠናው የተገባ ሲሆን ሥልጠናው ከፍተኛ ሞያ ባካበቱ በመንግስትና በግል የሚሠሩ ባለሞያዎች ሙሉ ሥልጠናው ተካሂዷል፡፡ተሰብሳቢዎችም ከፍተኛ የሆነ ተሳትፎ አድርገዋል ፡፡

ሥልጠናው በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት እና በአድባራትና ገዳማት የሚገኙ መሪዎችንና አገልጋዮችን የመሪነትና የሥራ ብቃት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ለታሰበው የአሠራር ለውጥ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የታቀደ ሥልጠና ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ስለ ሥልጠናው ዓላማ አስመልክቶ ሲናገሩ፣ ሀ/ስብከቱ በአስተዳደር፣ በፍትሕ መንፈሳዊ፣ በማኅበራዊ አገልግሎትና በምጣኔ ሀብት በኩል በሕግና ሥርዐት በመመላለስና በመደራጀት ውጤታማ ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡ በርካታ ዕቅዶቹን ተግባራዊ ለማድረግ በሀ/ስብከቱ የሚገኙ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በለውጡ አጀንዳዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በዘርፉ የላቀ ክህሎትና ዕውቀት ባላቸው ባለሞያዎች የሥልጠናና ምክክር መርሐ ግብሩን ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

ከሀ/ስብከቱ የሥራ ግዝፈትና ካለው ሰፊ የፋይናንስ ፍሰት አንጻር ሲመዘን ችግሩ የተጋነነና የገዘፈ እንዳልኾነ የሚያምኑት ብፁዕነታቸው፣ ተጠቃሽ ጉድለቶችን ሲዘረዝሩ፡-

1. የመልካም አስተዳደር ግድፈትና ማሽቆልቆል፣

2. ዘመኑን የዋጀ የምጣኔ ሀብት አስተዳደርና ዘመናዊ የሒሳብ አሠራር ክፍተት፣

3. የእርስ በርስ አለመናበብና የጎጠኝነት ስሜት፣

4. ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዐት አለመዘርጋት

5. የተአምኖ ግብርና እና የሥነ ምግባር ደረጃ ዝቅ ብሎ መገኘትና የመሳሰሉትን እንደኾኑ ጠቁመዋል፡፡ ብፁዕነታቸው እንዳብራሩት፣ መልካም አስተዳደር÷ ከእግዚአብሔር በተሰጠን ሥልጣንና ሓላፊነት የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት በሁሉም መስክ በጎ አርኣያነት ያለው መልካም እረኛ መኾን ማለት ነው፡፡ በመልካም አስተዳደር መርሕ መሠረት ‹‹ሓላፊ ነኝ፤ አዛዥ ነኝ›› ከሚል መኮፈስ ይልቅ የአገልጋይነትና የመሪነት ስሜት መላበስ ተገቢ ነው፡፡ ‹‹የምንመራትና የምናገለግላት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር በደሙ የዋጃት እንደመኾኗ መጠን የተቀበልነው አደራ እጅግ ታላቅና በልዑል እግዚአብሔር ፊት ቀርበን ዋናውን ከትርፍ ጋራ የምንጠየቅበት ነው፤›› ያሉት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ የምንመራቸው ሰዎችና የምናስተዳድረው ሀብት የእግዚአብሔር ሀብት ነውና ሓላፊነታችን እጅግ ከባድ እንደኾነና አገልግሎታችንም በዚሁ አቅዋምና መንፈስ ሊቃኝ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ ሐምሌ 9/2005 በተጀመረውና በ11/2005 የሚጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የሥልጠና መርሃ ግብር፡-

1. መልካም አስተዳደር እና ጠቀሜታው

2. የግዥ ሥርዐት፣ ተያያዥ ችግሮቹና የመፍትሔ አቅጣጫ

3. ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራር፣ አያያዝና ተጠያቂነት

4. የዕቅድ፣ ቁጥጥር፣ ክትትል እና ግምገማ ሥርዐት

5. ውጤታማ መሪነት ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት

6. ሙስናና ተያያዥ ችግሮች

7. የግጭት መንሥኤ እና አፈታት የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች የተካተቱ ሲኾን የዘርፉ ባለሞያዎችና ምሁራን ከቤተ ክርስቲያናችን ተጨባጭ ችግሮች ጋራ በማዛመድ በሚያቀርቧቸው መነሻዎች ተሳታፊዎቹ ውይይት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የአሁኑን ጨምሮ በሁለት ዙሮች ከሚካሄደው የሥልጠናና ምክክር ጉባኤ ጋራ በተያያዘ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት እና በአዲስ መልክ በተሠራው መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በሚቋቋሙት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የሓላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ የካሄዳል፡፡

ሀገረ ስብከቱ ቃል በገባው መሠረት ከሐምሌ 17/2005 በአዲሱ መዋቅር መሠረት ሙሉ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአዲሱ አደረጃጀት ሀ/ስብከቱ ለመልካም አስተዳደር በሚያመቹ ሰባት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲኾን በቋሚ ሲኖዶሱ ተሻሽሎ በጸደቀለት ልዩ መተዳደርያ ደንብ መሠረት በአግባቡና በሥርዓቱ ሥራውን መሥራት ያስችላል ይህ ልዩ ጊዚያዊ መተዳደርያ ደንብ እስከ ጥቅምት ወር ፳፻፮ ዓ.ም ብቻ በጊዜያዊነት የሚያገለግል ሲሆን የሥራ ምደባውም በትምህርት ዝግጅትና በአገልግሎት ዘመን እንደ ሆነ ለማውቅ ተችሏል፡፡ ይህን በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ሥራንና ሠራተኛን ለማገናኘት ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ በማስቀመጥ ሓላፊነትና ተጠያቂነት ያለው የአሠራር ሂደት በቁርጠኝነት እንደሚከተል የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የሥልጠናው መርሐ ግብር ዓላማ ባብራሩበት ወቅት አስረድተዋል፡፡

የኮርሱን ጽሑፍ ዳውንሎድ ያድርጉ (ውጤታማ መሪነት)

የኮርሱን ጽሑፍ ዳውንሎድ ያድርጉ (ሙስና)

የብፁዕነታቸውን ሙሉ ንግግር ከዚህ ቀጥሉ እንደሚከተለው ይቀርባል

ዝርዝር ንባብ...
 
ዓመታዊው የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል በድምቀት ተከበረ

5.5

በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው የሥላሴ በዓል በዚህ ዓመትም በመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡

በዚሁ ዕለት አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን የባረኩበት፣ የአንድነታቸውንና ሶስትነታቸው ሚስጢር የተገለፀበት ታላቅ በዓል ነው። በዓሉ መከበር የጀመረው ከዋዜማው ከሐምሌ6 ጀምሮ ሲሆን የካቴድራሉ ካህናትና መዘምራን ከዋዜማው ከቀኑ 3 ሰዓት ጀምሮ ለ30 ሰዓታት ያህል ሌሊትና ቀኑን ሙሉ ያለ ማቋረጥ ስብሃተ እግዚአብሔር ሲያቀርቡ ውለው አድረዋል፡፡

ይህመንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም ስርዓተማህሌተ፣ ስርዓተቅዳሴ እንዲሁም ሰዓታትና ሰርክ ፀሎት በአጠቃለይ የስርዓተ አምልኮ አፈፃፀም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ልዩ በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እጀግ በጣም የሚስደንቅ በዓል ነው፡፡

 

በሌላ ዜና የካቴድራሉ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ሰርቲፊኬት ሐምሌ 6/2005 ዓ.ም የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ በተገኙበት መርሃ ግብሩ ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ዕለት ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎችና ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች በካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሽልማት ተሰጧቸዋል፡፡

 
ዝርዝር ፅሁፍ...
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 10 ከ 19

የቤተክርስቲያን አድራሻ

የካቴድራሉ ሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤት
ስልክ ፤ 011-1-23-35-18 / 011-1-23-35-15
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
church@trinity.eotc.org.et
www.trinity.eotc.org.et

ግጻዌ

ማስታወቂያ

ለመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት የበኩልዎን አስታዋጽዖ ያድርጉ!

መርዳት የምትፈልጉ ምዕመናን ሁሉ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

አራት ኪሎ ቅርንጫፍ, ቁጥር= 0171859072600/2637 (መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት )

ብላች መላክ ትችላላችሁ፡፡